Skip to main content

መዳረሻ ቁልፌ የማይሠራ ከሆነስ?

የሚከተለው የስሕተት መልዕክት ከደረሰዎ፦ «መዳረሻ ቁልፍዎ ትክክል ያልሆነ ይመስላል። ይህ እንደገና ከተከሰተ እባክዎ የአገልግሎት አስተዳዳሪዎን ያነጋግሩ።» ለችግሩ መላ ለመፈለግ ከታች ያሉትን እርምጃዎች ይከተሉ፦

  1. በራስ-ሰር ወደ ቅንጥብ ሰሌዳው ላይቀዱ የሚችሉትን «ss://» የሚሉት የመጀመሪያ አምስት ቁምፊዎች ጨምሮ ሙሉውን መዳረሻ ቁልፍ ማስገባትዎን ያረጋግጡ። ሙሉ መዳረሻ ቁልፍ ምን እንደሚመስል ምሳሌ እነሆ (ናሙና ብቻ፤ አይሠራም)፦
ss://[email protected]:39485/?outline=1
  1. መዳረሻ ቁልፍዎ ጨርሶ ወደ ቅንጥብ ሰሌዳዎ የማይቀዳ ከሆነ ይህ በእርስዎ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ ወይም መሠረተ ሥርዓት ምክንያት ሊሆን ይችላል። በአብዛኛው ይህ የመከሰት ዕድል ያለው በእውቂያ ዝርዝርዎ ውስጥ ከሌለ ሰው መልዕክት ሲደርስዎት ነው። ኮዱን ከመልዕክት ላይ እየቀዱ ከሆነ ላኪው ወደ እርስዎ እውቂያዎች እንደታከሉ ያረጋግጡ፣ ከዚያም አገናኙን እንደገና ለመድረስ ይሞርኩ።
  2. እርምጃዎች 1 እና 2ን ካጠናቀቁ እና አሁንም የስሕተት መልዕክት የሚደርስዎ ከሆነ አገልጋዩ የታገደ ወይም መዳረሻ ቁልፉ ከእንግዲህ የማይሠራ የመሆን ከፍተኛ ዕድል አለው። የአገልጋይ አስተዳዳሪው ከሆኑ ለራስዎ አዲስ ቁልፍ ለማመንጨት ይሞክሩ። ይህ ካልሆነ አዲስ ቁልፍ እንዲደርስዎ የአገልጋይ አስተዳዳሪዎን ያናጋግሩ።