የኬላ ስሕተቶች
ሊያጋጥሙዎ የሚችሉ ሦስት የኬላ ችግሮች ዓይነቶች አሉ፦
እርስዎ በአውታረ መረብ ኬላ ሊታገዱ ይችላሉ።
እንደ ትምህርት ቤት ወይም መሥሪያ ቤትዎ ያለ ኬላ የተደረገበት አውታረ መረብ ጋር ተገናኝተው ሳለ Outlineን ለመጫን እየሞከሩ ከሆነ በተለየ አውታረ መረብ ላይ ሆነው ለመጫን ይሞክሩ።
ይህ የማይሠራ ከሆነ፣ እባክዎ ኬላ የተደረገበት አውታረ መረብ መካከል ያሉ ግንኙነቶችን ለOutline አገልጋይዎ እንዲፈቅዱ የአውታረ መረብ አስተዳዳሪዎን ያነጋግሩ። የOutline አገልጋይዎን አይ ፒ አድራሻ እና Outline የሚሄድባቸውን ወደቦች ማወቅ ይኖርብዎታል፣ እነዚህም የጭነት ስክሪፕቱ መጨረሻ ላይ የተመላከቱ ናቸው።
በመሣሪያ ኬላ ታግደው ሊሆን ይቻላል።
በመሣሪያዎ ላይ መደበኛ ባልሆኑ ወደቦች ላይ ወደ ውጭ የሚወጡ ግንኙነቶችን የሚያግድ ሶፍትዌር ወይም የማይትወቅ ሶፍትዌር (የCheckpoint ZoneAlarm) ካለዎት እባክዎ እንዴት ለOutline ልዩ ሁኔታ መፍጠር እንደሚቻል ለማወቅ የእርስዎን መሣሪያ ወይም ሶፍትዌር ሰነድ ይመልከቱ።
እርስዎ በአገልጋይ ኬላ ታግደው ሊሆን ይችላሉ።
የመረጡት የደመና አቅራቢ Outline የሚሄድባቸውን ወደቦች ለመክፈት ለአገልጋይ ኬላዎ ልዩ ሁኔታዎችን በእጅ እንዲፈጥሩ ሊጠይቅዎት ይችላል። የጭነት ስክሪፕቱን ካሄዱ በኋላ፣ Outline አገልጋይዎ ላይ የሚያሄድባቸው ሁለቱ በዘፈቀደ የተመረጡ ወደቦች ሊቀርቡልዎት ይገባ ነበር። እነዚህን ሁለት ወደቦች መክፈት በቂ መሆን አለበት።
ለእርስዎ የአገልጋይ ኬላ ልዩ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰነዱ ላይ «ufw» እና «iptables» የሚሉትን እንዲመለከቱ እንመክራለን፦