Skip to main content

ለምንድነው Outline አስተዳዳሪን በWindows ላይ መጫን የማልችለው?

ይህን የስሕተት መልዕክት ሊመለከቱ ይችላሉ፦ «ይቅርታ፣ Outline በአግባቡ ያልተጫነ ይመስላል። እባክዎ እንደገና ለመጫን ይሞክሩ። እሱ ካልሠራ እባክዎ ግብረመልስ ያስገቡ።»

Outlineን Windows ላይ እየተጠቀሙ ከሆነ፣ አልፎ አልፎ ያልተጠበቀ ስሕተት ሊያጋጥምዎት ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ፣ የOutline TAP አስማሚ (ነጂ) መሰረዝ ያስፈልገዋል እና Outline እንደገና መጫን ይኖርበታል።

እርምጃዎቹ በእርስዎ የWindows ሥርዓተ ክወና ሥሪት መሠረት ሊለያዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን TAP አስማሚ እና የOutline አስተዳዳሪን እንዴት ማራገፍ እና ከዚያም የOutline አስተዳዳሪን እንዴት እንደገና መጫን እንደሚቻል አጠቃላይ እርምጃዎች ከታች አሉ።

  1. ለOutline አስተዳዳሪ TAP አስማሚውን ያራግፉ
    1. ወደ የመሣሪያ አስተዳዳሪዎች፣ ከዚያ የአውታረ መረብ አስማሚዎች ይሂዱ
    2. የ«TAP-Windows Adapter V9 ፋይልን ወይም ከOutline ጋር የተጎዳኘ የTAP አስማሚን ያግኙ
    3. ይህን አስማሚ ያራግፉ ወይም ይሰርዙ። ይህ ሌሎች የጫኗቸው VPN መተግበሪያዎች ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ልብ ይበሉ።
  2. የOutline አስተዳዳሪን ያራግፉ
    1. ወደ ፕሮግራሞች እና ባህሪያት፣ ከዚያም ወደ ፕሮግራምን አራግፍ ይሂዱ
    2. የOutline አስተዳዳሪ መተግበሪያን ያግኙ እና የOutline አስተዳዳሪን ያራግፉ
    3. የOutline አስተዳዳሪ የቅርብ ጊዜ ሥሪትን ያውርዱ እና Windows መሣሪያዎ ላይ ዳግም ይጫኑት። አዲሱ ጭነት በራስ-ሰር አዲስ TAP አስማሚ መጫን አለበት።

አሁንም ችግር እያጋጠመዎ ከሆነ ድጋፍን ያነጋግሩ