Skip to main content

መሣሪያዎን ከOutline አገልጋይ ጋር ማገናኘት

መሣሪያዎን ከOutline አገልጋይ ጋር ማገናኘት

መሣሪያዎን ከOutline አገልጋይ ጋር ለማገናኘት፣ የአገልጋይ አስተዳዳሪ እርስዎ ከአገልጋያቸው ጋር እንዲገናኙ ልዩ የመዳረሻ ቁልፍ ያለው ግብዣ ሊልኩልዎት ይገባል። ይህ ግብዣ፦

  • ቀድሞውኑ ከሌለዎት በመሣሪያዎ ላይ Outline እንዲያወርዱ እና እንዲጭኑ ይጠይቅዎታል
  • በእርስዎ እና በOutline አገልጋዩ መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ለማድረግ የመዳረሻ ቁልፉን ይጠቀማል

ከአገልጋዩ ጋር ያለዎትን ግንኙነት አንዴ ከመሠረቱ በኋላ Outline ለመጠቀም «አገናኝ» ወይም «አቋርጥ» የሚለውን ጠቅ ማድረግ ይችላሉ።

አስፈላጊ፦ Outline ያለ የመዳረሻ ቁልፍ እና የOutline አገልጋይ አይሠራም። የOutline መተግበሪያን ያለ ቁልፍ ማውረድ እና መጫን የበይነመረብ ትራፊክዎን ደህንነት አይጠብቅም።