Skip to main content

የOutline አገልጋይ ውቅረት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

Outlineን ያለአገልጋይ መጠቀም እችላለሁ?

እንደ አለመታደል ሆኖ፣ አይቻልም። የOutline ሶፍትዌር በእርስዎ የሚተዳደርም ሆነ በድርጅትዎ ወይም ደግሞ በታማኝ የሦስተኛ-ወገን የአገልጋይ መዳረሻ ይፈልጋል።

የOutline አገልጋይን ለማዋቀር ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

አብዛኛውን ጊዜ፣ ከ5 ደቂቃዎች ያነሰ። Outlineን በማንኛውም የደመና አገልጋይ ላይ መጫን ይችላሉ፣ ነገር ግን እኛ ያለምንም ስክሪፕቶች አገልጋይዎን በጥቂት ጠቅታዎች ማዋቀር የሚችሉበት የበለጠ ለተጠቃሚ ተስማሚ፣ በመመሪያ የሚመራ የጭነት ተሞክሮ ለማቅረብ ከDigitalOcean ጋር ሠርተናል።

AWS፣ GCP ወይም የላቀ ውቅረትን ከመረጡ፣ የአገልጋይ ጭነት ሂደቱን አብዛኞቹን አካባቢዎች ወደሚይዘው ነጠላ ስክሪፕት አቅልለነዋል።

የOutline አገልጋይን የት ማዋቀር እችላለሁ?

የOutline አገልጋይን የትም ቦታ ቢሠሩ በአብዛኞቹ የደመና አቅራቢዎች ላይ ማዋቀር ይችላሉ።

እንደ አምስተርዳም፣ ቶሮንቶ፣ ሳን ፍራንሲስኮ እና ሲንጋፖር ባሉ በርካታ አካባቢዎች ላይ አገልጋዮች ስላሉት ቀላሉ አማራጭ DigitalOcean ላይ ማዋቀር ነው። ሌላ የደመና አቅራቢ ላይ ወይም የራስዎ መሠረተ ልማት ላይ ለመጫን ከመረጡ የOutline አስተዳዳሪ መተግበሪያ ላይ «የላቀ ሁነታ»ን መምረጥ እና የማዋቀሪያ ስክሪፕትን በመጠቀም የጭነት መመሪያዎችን መከተል ይችላሉ።

የእኔን የOutline አገልጋይ የት ማዋቀር አለብኝ?

  1. ለእርስዎ የOutline አገልጋይ አካባቢ ሲመርጡ ጥቂት ከግምት ውስጥ ማስገባት ያለብዎት ነገሮች አሉ፦
  2. የOutline አገልጋይ አካባቢ ተጠቃሚዎች በይነመረብ ላይ የሚኖራቸው ተሞክሮ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ለምሳሌ፣ አገልጋዩ የሚገኘው አምስተርዳም ከሆነ፣ ይህንን አገልጋይ የሚደርስበት ተጠቃሚ ኔዘርላንድ ውስጥ በአካል እንደሚገኝ ያህል የበይነመረቡ ተሞክሮ ይኖረዋል። አንዳንድ ድር ጣቢያዎች በደች ሊያሳዩ ሁሉ ይችላሉ። በተለምዶ፣ ድር ጣቢያው ላይ ባለው የቋንቋ መራጭ የአካባቢውን ቋንቋ መሻር ይችላሉ።
  3. በእርስዎ ተጠቃሚዎች እና በOutline አገልጋዩ መካከል ያለው ርቀት ፍጥነቶችዎ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። በአጠቃላይ፣ በየOutline ተጠቃሚዎች እና በአገልጋዩ መካከል ያለው አካላዊ ርቀት የተጠቃሚዎች የበይነመረብ ፍጥነቶች ልይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ፣ የሚጠበቁት ተጠቃሚዎች ከሚገኙበት ቅርብ የሆነውን የአገልጋይ አካባቢ መምረጥ ይችላሉ፣ ነገር ግን የትኛዎቹ የበይነመረብ ገመዶች ከእርስዎ አገር ወይም ክልል ጋር እንደተገናኘ ለማየት ሰርጓጅ የገመድ ካርታን መመልከት ይችላሉ።
  4. የእርስዎ የVPN አገልጋይ የሚገኝበት ቦታ የሕግ ማዕቀፉ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። እባክዎ የOutline ሶፍትዌር የእርስዎን ትራፊክ መዝግቦ እንደማያስቀምጥ ልብ ይበሉ። Outlineን በሚጠቀሙ ጊዜ ሰለ ደህንነት እና ግላዊነት የበለጠ ይወቁ።